ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ፅዱ ውብና ለኑሮ ተስማሚ...

image description
- In pulice partspation    0

ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ፅዱ ውብና ለኑሮ ተስማሚ የሆነች ከተማን ለመፍጠር በትኩረት ተሰርቷል ሲሉ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ ተናገሩ ህዳር 20/2018

የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በየሳምንቱ ቅዳሜ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚያከናወነው ብሎክን መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር  በሁሉም ክ/ከተሞች ያካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በልደታ  ክ/ከተማ ወረዳ 10 ቢርሞ ሜዳ አካባቢ ደግሞ በድምቀት አካሂዷል።

በዚሁ ንቅናቄ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ እንደተናገሩት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ፅዱ ውብና ለኑሮ ተስማሚ የሆነች ከተማን ለመፍጠር በትኩረት መሰራቱን ጠቁመወ በተሰራው ስራም በከተማዋ ፅዳት ዙሪያ ተጨባጭ ለውጥ መምጣት መቻሉን አብራርተዋል።

አቶ ገዛኸኝ አክለውም ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር የቤት ለቤት ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራም ጭምር ሲሰራ ነበረ ብለው በዚህም ውብ ፅዱና ለኑሮ ተስማሚ ከተማን እየፈጠርን ነው በማለት ተናግረዋል።

ማህበረሰቡ ውብና ፅዱ ከተማ ለመፍጠር ፅዳትን ከግቢው መጀመር አለበት ያሉት አቶ ገዛኸኝ ማህበረሰቡ ከፅዳት ባለፈ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓቱንም እንዲያሻሽል ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ህዳርን በጽዳት እስከ ህዳር 30 የሚቀጥል ስለመሆኑና ቆሻሻ በማቃጠል ሳይሆን ቆሻሻን በማጽዳት የከተማዋን ጽዳትና ውበት ለማስጠበቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል

የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ በበኩላቸው ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ እየፈጠርን ከተማችን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን እየሰራን ነው ብለው በዚህም አበረታች ውጤቶችን አስመዝግበናል በማለት ገልፀዋል።

አቶ አሰፋ አክለውም መንግስት የግንዛቤ ስራውን በማጠናከር ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ከማድረግ ባለፈ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትም እንዲሻሻል ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ሲሉ ገልፀዋል።

ስማርት ሲቲን ለመገንባት የተያዘው ስራ እንዲሳካ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓታችንን የማዘመን ስራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ አሰፋ ገልፀዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያየህ ዓለም እንደተናገሩት ንፁህ አካባቢን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራን ነው ብለው በዚህም ቆሻሻን የሚፀየፍ ትውልድ እየገነባን ነው በማለት ገልፀዋል።

ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ትውልድ ለመፍጠር በትምህርት ተቋማትም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ያየህ ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments