ኤጀንሲው በሁለተኛው ሩብ ዓመት የ3 ተከታታይ ሳ...

image description
- In Uncategorized    0

ኤጀንሲው በሁለተኛው ሩብ ዓመት የ3 ተከታታይ ሳምንታት ድጋፍና ክትትል ስራዎች አፈፃፀምን ገመገመ ህዳር 23/2018ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮች እና ጠቅላላ ካወንስል አባላት በበጀት ዓመቱ ሁለተኛ ሩብ ዓመት በሶስት ተከታታይ ሳምንታት የተከናወኑ የድጋፍና ክትትል ስራዎች አፈፃፀም በጋራ በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

 

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በግምገማ መድረኩ ላይ እንደገለጹት በሁለተኛው ሩብ ዓመት ሶስት ተከታታይ ሳምንታት የተከናወኑ የመደበኛ እና የድጋፍና ክትትል ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀም በበጀት ዓመቱ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት በሚያስችል መልኩ ውጤት የተመዘገበባቸው እንደሆነ ገልፀዋል።

 

አቶ ገዛኸኝ አክለውም ውጤትን ማዕከል ያደረገ የግምገማ ሥርዓት በመዘርጋት፣ አመራርና ፈፃሚን በተደራጀ መንገድ ወደ ስምሪት በማስገባት ችግሮችን ለመፍታትና ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልፀው በቀጣይም በድጋፍና ክትትሉ  የተገኙ ስኬቶችን  ለማስቀጠልና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

 

በቀጣይ ቀሪ ቀናቶችም ተቋማትን ጨምሮ በሁሉም ክ/ከተሞች እስከ ብሎክ የዘለቀ የፅዳት ንቅናቄ ስራው  ህብረተሰቡም ቆሻሻን በአይነት በመለየት በአግባቡ እንዲይዝ እና የፅዳት ስራው ተቋማዊና ባህል እንዲሆን ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ የገንዛቤ ስራዎች  እንዲሁም አገልግሎቶችን በተቀመጠላቸው መስፈርት መሰረት ከመፈፀም አንፃር፣ ህገወጥነትን መከላከል እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ተግባራት  ግለቱን ጠብቆ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

 

አቶ ገዛኸኝ በማጠቃለያ ንግግራቸው እንደተናገሩት

በርካታ ስራዎች በጥራትና በፍጥነት የተሰሩ ቢሆንም፣ የተሰሩ ስራዎችን ሰብስቦና አደራጅቶ መረጃ ከማድረግ አንፃር ግን ክፍተት መኖሩን እና ለወደፊትም መስተካከል እንዳለበት አሳስበዋል።

 

ይህ ክፍተት የስራ ውጤቶችን በግልጽ ለመመዘን፣ ለቀጣይ እቅድ ዝግጅት እና ለተጠያቂነት ስርዓት ግንባታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸው፣ በቀጣይ የመረጃ አያያዝ ስርአትን ማጠናከር  ላይ ልዩ ትኩረት እንደሚያስፈልገው አብራርተዋል።

 

ከተሳታፊዎችም ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች ላይም ከመድረክ ምላሽ በመስጠት እና በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ተግባራት ላይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments